የስያትል ኮቪድ-19 (COVID-19) ስደተኞች ኣስቸኻይ እርዳታ ፈንድ

ማመልከቻዎችን ከአሁን በኋላ አንቀበልም፡፡

የሽልማት ዉሳኔዎች (ተፈቅዷል ወይንም ተከልክሏል)፡ ከኖቬምበር 23 ቀን 2020 እስከ ኖቬምበር 30 ቀን 2020 ድረስ
ክፍያ የሚፈጽምበት፡ ከዲሴምበር 1 ቀን 2020 በኋላ
እንዲሁም ለዋሽንግተን ስቴት ፈንድ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ www.immigrantreliefwa.org.
የስያትል ኮቪድ-19 (COVID-19) ስደተኞች ኣስቸኻይ እርዳታ ፈንድ የ $7,900,000 ቀጥታ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ በጣም ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ስደተኛ ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸዉ የተዘጋጀ የገንዘብ ድጋፍ ነዉ። ይህ ፕሮግራም ቅድሚያ የሚሰጠዉ ለፌደራል ኮሮናቫይረስ እርዳታ፣ እፎይታ፣ ና ኢኮኖሚ ደህንነት ደንብ (CARES Act) ክፍያዎች (“የኮሮናቫይረስ ማነቃቅያ ቼክ”) ና ለስቴቱ የሥራ አጥ ኢንሹራንስ በኢሚግሬሽን ሁኔታቸዉ ምክንያት ብቁ ላልሆኑ አማልካቾች ነዉ።

የጊዜ ሰሌዳ

 • ማመልከቻ ክፍት የሚሆንበት ወቅት፡ 3 ሳምንታት ከሀሙስ ኦክቶበር 15 ቀን 2020 እስከ ኖቬምበር 5 ቀን 2020 ድረስ
 • የማመልከቻ ክለሳ ወቅት፡ 2 ሳምንታት ከኖቬምበር 9 ቀን 2020 እስከ ኖቬምበር 22 ቀን 2020 ድረስ
 • የሽልማት ዉሳኔዎች (ተፈቅዷል ወይንም ተከልክሏል)፡ ከኖቬምበር 23 ቀን 2020 እስከ ኖቬምበር 30 ቀን 2020 ድረስ
 • ክፍያ የሚፈጽምበት፡ ከዲሴምበር 1 ቀን 2020 በኋላ

በቤተሰብ የሚሸጠዉ የሽልማቱ መጠን እንደ ቤተሰቡ አባላት ቁጥር፡

 • $1,000 - $3,000

የግላዊ መረጃ ፖሊሲ ማጠቃለያ

ለትርፍ የማይሠራዉ Scholarship Junkies ድርጅት ለሲያትል ለስደተኞች COVID-19 እፎይታ ፈንድ የኦንላይን ማመልከቻ በፈቃድዎ የምታስገቡትን የግል መረጃ ለመሰብሰብ ኃላፍነት ወስዷል። Scholarship Junkies የመረጃዎን ደህንነት ለመጠበቅ አግባብ ያለዉ አካላዊ፣ የኤሌክትሮኒክ ና አስተዳደራዊ አካሄዶችን አቋቁሟል። የሲያትል ከተማን ጨምሮ መረጃዎትን ከመንግስት አካላት ጋር በፈቃደኝነት አያጋሩም።

Application Assistance

Please refer to our Language Assistance Guide if you need help in a language other than Amharic, Cantonese, Mandarin, Korean, Somali, Spanish, Tagalog, and Vietnamese.

Información del contacto

Si necesita ayuda con la solicitud, llame al:
Alguien que hable español le ayudará o puede que le conecten con un intérprete externo.

联系信息

如果您需要帮助填写申请,请致电:
会讲中文的工作人员将帮助您,或者您可能会被连接到第三方口译员。

Impormasyon sa Pakikipag-ugnayan:

Kung kailanganin ninyo ng tulong sa aplikasyon, mangyaring tumawag sa
May makakatulong sa inyo na nagsasalita ng Tagalog o di kaya nama'y ikokonekta kayo sa ibang tagapagsalin sa Tagalog.

연락처 정보:

신청과 관련하여 도움이 필요하시면
 • Korean Community Service Center (한인 생활 상담소): 425-776-2400 로 전화하세요.
한국어를 구사하는 직원에게 도움을 받거나 제3자 통역사와 연결될 수 있습니다.

የማግኛ መረጃ

ለዚህ ማመልከቻ ድጋፍ ከፈለጉ እባክዎን
አማርኛ የሚናገር ሰዉ ድጋፍ ይሰጥዎታል ወይንም ከሶስተኛ ወገን አስተርጓሚ ጋር ይገናኛሉ።

Xiriirka macluumaadka:

Haddii aad u baahan tahay in lagaa caawiyo arjiga, fadlan wac:
Qof ku hadla [LUQADAADA] ayaa kaa caawin doona ama waxaa lagaa yaabaa in lagugu xirno dhinaca sadexaad oo ah turjubaan.

Thông Tin Để Liên Lạc

Nếu quý vị cần giúp điền đơn hay thắc mắc về xin tiền hỗ trợ hãy vui lòng gọi:
Một người nào đó nói tiếng Việt sẽ hỗ trợ quý vị hoặc nhân viên sẽ kết nối với thông dịch viên.

If you do not see your language you can call: 206-503-0657. When you call, please inform us what language you speak, and wait as we will likely need to connect with an interpreter.

የማህበረሰብ አጋሮች

በተቻለ መጠን ለብዙዎች አስቸኳይ የገንዘብ እፎይታ ለመስጠት በጋራ እየሰራን ነው ፡፡

FAQ

የስያትል ኮቪድ-19 (COVID-19) ስደተኞች ኣስቸኻይ እርዳታ ፈንድ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

1. ለሲያትል ለስደተኞች COVID-19 እፎይታ ፈንድ ለማመልከት ብቁ መሆኔን እንዴት ለማወቅ እችላለሁ?

እባክዎን “የብቁነት” ክፍል ከላይ ይመልከቱ።

2. ማመልከቻዎች መግባት ያለባቸዉ መቼ ነዉ?

የማመልከቻ ጊዜ የሚከፈተዉ ሀሙስ ኦክቶበር 15 ቀን ከጧቱ 8:00 AM ሰዓትና የሚዘጋዉ ሀሙስ ኖቬምበር 5 ከሌሊቱ 11:59 PM ነዉ። ማመልከቻዎን በዚህ ወቅት በማንኛዉም ሰዓት ማስገባት ይችላሉ። ዘግይተዉ የገቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት የላቸዉም።

3. ምን ዓይነት ሰነዶችን ነዉ ማስገባት ያለብኝ?

ማንነትዎንና የሲያትል ነዋሪነትዎን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይፈለጋሉ። ከዚህ በታች ያለዉ ሠንጠረዥ መጠቀም የምትችሏቸዉ ሰነዶች ምሳሌዎች አቅርቧል።

[ዝርዝር A]
የመኖሪያና መታወቅያ ሰነዶች

[ዝርዝር B]
የመታወቅያ ሰነዶች

[ዝርዝር C]
የመኖሪያ ሰነዶች

 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የዋሽንግተን ስቴት መታወቅያ ካርድ
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የዋሽንግተን ስቴት መንጃ ፍቃድ
 • ሲያትል ዉስጥ ካለ ትምህርት ቤት የተሰጠ የአሁን የተማሪ መታወቅያ ካርድ
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የግልጋሎቶች ክፍያ ደረሰኝ
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የእጅ ስልክ ወይንም ኢንተርኔት ክፍያ ደረሰኝ
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የኢንሹራንስ ሕሳብ ዝርዝር
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የባንክ ሂሳብ ዝርዝር
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የ 2019 የገቢ ቀረጥ መመለሻ (ታክስ ርተርን)
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል መኖሪያ አድራሻዎን ወይንም የሲያትል ቀጣሪ አድራሻ የሚያሳይ የመስሪያ ቤት የደመወዝ ክፍያ ደረሰኝ
 • የየትኛዉም ትምህርት ቤት የተማሪ መታወቅያ ካርድ
 • የየትኝዐዉም አገር ፓስፖርት
 • የቆንስላ ካርድ
 • የምዝገባ ማረጋገጫ ደብዳቤ ሲያትል ዉስጥ ካለ ትምህርት ቤት
 • ሙሉ ስሞንና የሲያትል አድራሻዎን የሚያሳይ የኪራይ ደረሰኝ
*ከሚከተሉት ተቋማት የደብዳቤ ጸሓፊዉ ሙሉ ስምና ስልክ ቁጥር ያለበት ተፈርሞ ቀን የተጻፈበት ደብዳቤ፡
 • የቤት አከራይ ሲያትል ነዋሪነትን ያረጋገጠበት
 • ሲያትል ዉስጥ ያለ ቀጣሪ አሁን ወይንም ቀድም ብሎ በመስሪያ ቤቱ መቀጠርዎን ያረጋገጠበት
 • ሲያትል ዉስጥ ካለ ትምህርት ቤትዎ ዉስጥ ያለ ሠራተኛ መመዝገብዎን ያረጋገጠበት
 • አገልግሎቶች አቅራቢ ወይም ጉዳይ የምይስተዳድር ድርጅት ሠራተኛ ሲያትል ነዋሪነትን ያረጋገጠበት
 • የአምልኮ ቦታዎ ተወካይ ሲያትል ነዋሪነትን ያረጋገጠበት

[List B]
Documents for Confirming Your Identity

[List C]
Documents Confirming Your Seattle Residency

*ይህን የዚህን ደብዳቤ ቅርጸት ለዚህ ማመልከቻ መጠቀም ይችላሉ።

4. ያመለከተ ሰዉ ሁሉ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል?

በፈንዱ ዉስንነት ምክንያት ሁሉንም ልናገለግል አንችልም። አንዳንድ ብቁ የሆኑ ኣመልካቾች የገንዘብ ድጋፉን ላይቀበሉ ይችላሉ።

5. ብቁ የሆኑ ኣመልካቾች እንዴት ነዉ የሚመረጡት?

በፈንዱ ዉስንነት ምክንያት ሁሉንም ልናገለግል አንችልም። የማየቱ ሂደት ቅድሚያ የደረሰ ቅድሚያ አገልግሎት ያገኛል በሚል መርህ አይደለም። የበለጠ የሚያስፈልጋቸዉን ለመርዳት ከዚህ በታች ባሉት በምንም ዓይነት ቀደም ተከተል ያልተዘረዘሩ መስፈርቶች መሠረት ኣመልካቾችን ቅድሚያ እንሰጣለን፡

 • ነጠላ ወላጆች/ተንከባካቢዎች።
 • መኖሪያ ቤት ሁኔታ።
 • የገንዘብ ፍላጎት።
 • የዋሽንግተን ስቴት የሥራ አጥ ክፍያ ማግኘት መቻል Access to Washington State Unemployment Benefits።
 • በ COVID-19 በሽታ የከፋ ህመም ስጋት።
 • ከቤተሰብ ጠብ፣ ጾታዊ ጥቃት ወይንም ሰዎች ህገወጥ ዝዉዉር እያገገሙ ያሉ።

6. እኔና የቤተሰቤ አባላት የህብረተሰብ ዕዳ ልንሆን እንችላለን ብለን መስጋት አለብኝ?

እንደ የዩኤስ ዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS) እንደዚህ ፕሮግራም ያሉ "የአደጋ እፎይታ" ክፍያዎችን አንድ ግለሰብ የህብረተሰብ ዕዳ መሆኑን ለመወሰን ከግምት አያስገቡም። ይህን የUSCIS ህብረተሰብ ዕዳ የጭብጥ ገጽ ለበለጠ መረጃ ማንበብ ይችላሉ። ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎና/ወይንም የክፍያዎች ጠቀሜታ ጥያቄዎች ካለዎት ከ ኢሜግሬሽን ጠበቃ ወይንም በፍትህ ምንስቴር የታወቀ ተወካይ ማናገር አለቦት።

7. ይህን የገንዘብ ድጋፍ መቀበል በቤተሰቤ አባላት ወይንም በኔ የአሜሪካ ዜጋ መሆን ላይ ተጽህኖ ያሳድራል?

ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ / አረንጓዴ ካርድ ያዥ ከሆኑ ከሲያትል ለስደተኞች COVID-19 እፎይታ ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ መቀበልዎ የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ብቃትዎ ላይ ተጽህኖ አይኖረዉም። የህጋዊ ቋሚ ነዋሪ / አረንጓዴ ካርድ ያዥ ቤተሰብ አባል የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ብቃት ላይም ተጽህኖ አይኖረዉም። ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎና/ወይንም የክፍያዎች ጠቀሜታ ጥያቄዎች ካለዎት ከ ኢሜግሬሽን ጠበቃ ወይንም በፍትህ ምንስቴር የታወቀ ተወካይ ማናገር አለቦት።

8. በዚህ ማመልከቻ ዉስጥ የምሰጠዉ መረጃ በምስጢር ይያዛል?

ለትርፍ የማይሠራዉ Scholarship Junkies ድርጅት ለሲያትል ለስደተኞች COVID-19 እፎይታ ፈንድ የኦንላይን ማመልከቻ በፈቃድዎ የምታስገቡትን የግል መረጃ ለመሰብሰብ ኃላፍነት ወስዷል። ያልተፈቀደለት እንዳይደርስበት ለመከላከል፣ የመረጃ ትክክለኛነትን ለመጠበቅ፣ መረጃ በትክክል ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ Scholarship Junkies የሰበሰቡትና መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ አግባብ ያለዉ አካላዊ፣ የኤሌክትሮኒክና አስተዳደራዊ አካሄዶችን አቋቁሟል። የሲያትል ከተማን ጨምሮ መረጃዎትን ከመንግስት አካላት ጋር በፈቃደኝነት አያጋሩም። ስለ Scholarship Junkies ጠቅላላ የግላዊ መረጃ ፖሊሲ የበለጠ ከዚህ ማወቅ ይችላሉ (በእንግልዝኛ ብቻ)።

9. ኮምፒዩተር ወይንም ኢንተርኔት የለኝም። ለማመልከት ሌሎች አማራጮች አሉኝ?

በዚህ የኦንላይን ፖርታል ብቻ ነዉ ከኢንተርኔት ጋር በተገናኘ ኮምፒዩተር ወይንም ተንቅሳቃሽ መሣሪያ መሙላት የምትችሉትን ማመልከቻዉ ማቅረብ የምንችለዉ። የኛ ሸሪክ ድርጅቶች በስልክ ድጋፍ እየሰጡና ከኢንተርኔት ጋር የተገናኘ መሣሪያ ከሌላዎት በማመልከት ሊረድዎት ይችላሉ። እባክዎን ለድጋፍ ከዚህ በታች ያሉትን ድርጅቶችን ያግኙ። እባክዎ አንድ ሰነድ ከዝርዝር  A ወይንም አንድ ሰነድ ከሁለቱም ዝርዝር B  ና ዝርዝር  C እንዳለዎት ያረጋግጡ፡

 • Community Response Alliance: 206-618-5794

10. ክፍያዎቹ ምን ያህል ነዉ?

 • አንድ አዋቂ የ $1,000 የአንድ ግዜ ክፍያ ሊቀበል ይችላል።
 • ጥንድ (ሁለት አዋቂዎች) የአንድ ጊዜ ቢበዛ $2,000 ክፍያ ለመቀበል ብቁ ናቸዉ።
 • ልጆች ያላቸዉ ጥንዶች፣ ወላጆች፣ ወይንም ተንከባካቢዎች የአንድ ጊዜ $3,000 ክፍያ ለመቀበል ብቁ ናቸዉ።

11. ይህ ያንድ ጊዜ ክፍያ ነዉ?

ብቁ የሆኑ አማልካቾች የአንድ ጊዜ ክፍያ ብቻ ነዉ ለመቀበል የምችሉት።

12. ክፍያዬን ለመቀበል ምን ያህል ጊዜ ይውስዳል?

ጥያቄ #13 ይመልከቱ።

13. ክፍያዬን እንዴት ነዉ የምቀበለዉ?

ክፍያዎችን ለመቀበል አራት አማራጮች አሉ፡

አማራጭ

ክፍያ ለመቀበል ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

ክፍያዉን እንዴት ነዉ የምቀበለዉ?

ቼክ*
የማመልከቻ ወቅት ካበቃና ለመስጠት ዉሳኔ ከተደረገ 7-14 ቀናት በኋላ።
በፖስታ በፖስታ አገልግሎት ወደ ሰጣቹት የፖስታ መላኪያ አድራሻ
ቁሳዊ ማስተር ካርድ የስጦታ ካርድ**
የማመልከቻ ወቅት ካበቃና ለመስጠት ዉሳኔ ከተደረገ 7-14 ቀናት በኋላ።
በፖስታ በፖስታ አገልግሎት ወደ ሰጣቹት የፖስታ መላኪያ አድራሻ
የዲጂታል ማስተር ካርድ የስጦታ ካርድ
የማመልከቻ ወቅት ካበቃና ለመስጠት ዉሳኔ ከተደረገ 1-2 ቀናት በኋላ።
በኢሜል በሰጣቹት ኢሜል አድራሻ
ቀጥታ ወደ ባንክ መላክ
የማመልከቻ ወቅት ካበቃና ለመስጠት ዉሳኔ ከተደረገ 2-5 ቀናት በኋላ።
ወደ ሰጣቹት ቀጥታ ወደ ባንክ አካዉንት በማስተላለፍ

*የወረቀት ቼኮች ከ90 ቀናት በኋላ ዋጋ የላቸዉም።

**ቁሳዊ ማስተር ካርድ የስጦታ ካርዶች ከ12 ወራት በኋላ ዋጋ የላቸዉም።

14. ከሲያትል ከተማ ወሰን ዉጪ ነዉ የምኖረዉ። ማመልከት እችላለሁ?

አዎ. ከሲያትል ዉጪ የሚኖሩ ከሆነ ማመልከት ይችላሉ፤ ሆኖም ግን እርስዎ ወይንም ከቤተሰብዎ አንድ ሰዉ በሲያትል ከተማ ክልል ዉስጥ የሚሠራ ከሆነ ወይንም ትምህርት ቤት የሚከታተል ከሆነ ብቻ ነዉ።

15. ያለተመዘገብኩ ነኝ። ክፍያ ለማግኘት ብቁ ነኝ?

ይህ ክፍያ ለማንኛዉም ለፌደራል ኮሮናቫይረስ እርዳታ፣ እፎይታ፣ ና ኢኮኖሚ ደህንነት ደንብ (CARES Act) ክፍያዎች ብቁ ላልሆነ ሰዉ ነዉ የታሰበዉ (ጥያቄ #1 ይመልከቱ)። በ ደንብ 121063 መሠረት የሲያትል ከተማ ማንኛዉንም ሰዉ የኢሚግሬሽን ሁኔታ መጠየቅ አይፈቀድለትም። ይህ ማለት በሲያትል ለስደተኞች COVID-19 እፎይታ ፈንድ ማመልከቻ ቅጽ ዉስጥ ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታ አንጠይቅም ማለት ነዉ።

16. ባለትዳር ነኝና ባለቤቴም እኔም ለክፍያዉ ብቁ ነን። ሁላታችንም ማመልከት አለብን?

አንዳችሁ ብቻ ናችሁ ለቤተሰባችሁ ማመልከት ያለበችሁ። ጥንድ (ሁለት አዋቂዎች) የአንድ ግዜ ቢበዛ $2,000 ክፍያ ለመቀበል ብቁ ናቸዉ።

17. ቤተሰቤ ብዙ ቤተሰቦችን ያቀፈ ነዉ። እንዴት ማመልከት አለብን?

እያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ ማመልከቻ ለዚያ ቤተሰብ ማስገባት አለበት።

18. ቤተሰቤ ብዙ ላጤ አዋቂዎችን ያቀፈ ነዉ። እንዴት ነዉ ማመልከት ያለብን?

እያንዳንዱ አዋቂ ለራሳቸዉ አንድ ማመልከቻ ማስገባት አለባቸዉ።

19. ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆቼን ወክዬ ማመልከት እችላለሁ?

አዎ. እርስዎ በጥያቄ #1 ስር በተዘረዘረዉ መስፈርት መሠረት ብቁ እስከሆኑ ድረስ ልጆች ማመልከቻዎ ወስጥ መካተት አለባቸዉ።

20. የልጆች ተንከባካቢ ነኝ። ለነሱ ማመልከት ወይንም የኔ ማመልከቻ ላይ እነሱን መጨመር እችላለሁ?

አዎ. የራስዎ የወለዱት፣ ያሳደጉት፣ ወይንም የእንጄራ ልጅ ያልሆነ ተንከባካቢ ወይንም ሞግዚት ከሆኑ ልጁ ለፈንዱ ብቁ እስከሆነ ድረስ ልጁን ወክሎ የተለየ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ።

21. ሲያትል ዉስጥ እየኖርኩ አይደለም። የቀድሞ የሥራ ቦታዬ ሲያትል ዉስጥ ነበር። እስካሁንም ሥራ የለኝም። ማመልከት እችላለሁ?

አዎ. ከሲያትል ከተማ ዉጪ የሚኖሩ ከሆነና ከ ጃኑዋሪ 1 2020 እስከ ሴምቴምበር 30 2020 ድረስ ባለዉ ግዜ የቀድሞ የሥራ ቦታዎ ሲያትል ከተማ ዉስጥ ከነበረ ማመልከት አለቦት። የቀድሞ የሥራ ቦታዎ ሲያትል ዉስጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማስገባት አለቦት። ለተፈቀዱ ሰነዶች ዝርዝር ጥያቄ #3 ይመልከቱ።

22. በአሁኑ ሰዓት ቋሚ ቤት የለኝም። ማመልከት እችላላሁ፤ እንዴት የገንዘብ ድጋፍ መቀበል እችላለሁ የፖስታ አድራሻ ሳይኖራኝ?

አዎ. ቋሚ መኖሪያ ቤት የሌላቸዉ ብቁ አማልካቾች ማመልከት አለባቸዉ። ሁለት አማራጭ ኣሎት፡

I. ብቁ ከሆኑና ኢሜል ካለዎት በዲጂታል ስጦታ ካርድ ፈንዱን መቀበል ይችላሉ።

II. ብቁ ከሆኑና ቼክ ወይንም ስጦታ ከርድ ራሱን መቀበል ከፈለጋችሁ የኛ ሽርክ ድርጅቶች ልራዷችሁ ይችላሉ። ለምሳሌ የድርጅትን ፖስታ አድራሻ ቼኩን ለመቀበል መጠቀም ይችላሉ። እባክዎን ለድጋፍ ከዚህ በታች ካሉት ድርጅቶች አንዱን ያግኙ፡

 • Community Response Alliance: 206-618-5794

23. በምንም ምክንያት ይሁን ከሲያትል ለስደተኞች COVID-19 እፎይታ ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ መቀበል ካልቻልኩ ሌሎች አማራጮች አሉ?

የዋሽንግተን ስቴትም ተመሳሳይ የገንዘብ እርዳታ ፕሮግራም እየሰጠ ነዉ፤ የስደተኞች እፎይታ ፈንድ። እዚህ ማመልከት ይችላሉ። ሌሎች ከ COVID-19 ጋር የተገናኙ የድጋፍ ፕሮግራሞች የሲያትል ከተማ COVID-19 ማህበረሰብ ድጋፍ ምንጮችን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ፡ seattle.gov/covid-19

24. ኣመልክቼ ከሲያትል ለስደተኞች COVID-19 እፎይታ ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ ካላገኘሁ የይግባኝ ሂደት አለ?

ከሚጠበቀዉ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ አመልካቾች ምክንያት የይግባኝ ሂደት የልም። የዋሽንግተን ስቴትም ተመሳሳይ የገንዘብ እርዳታ ፕሮግራም እየሰጠ ነዉ፤ የስደተኞች እፎይታ ፈንድ። እዚህ ማመልከት ይችላሉ። ሌሎች ከ COVID-19 ጋር የተገናኙ የድጋፍ ፕሮግራሞች የሲያትል ከተማ COVID-19 ማህበረሰብ ድጋፍ ምንጮችን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ፡ seattle.gov/covid-19

25. የስያትል ኮቪድ-19 (COVID-19) ስደተኞች ኣስቸኻይ እርዳታ ፈንድ እንዴት ነዉ ገንዘብ የሚያገኘዉ?

ነሓሴ 21 2020 ከንቲባ Jenny Durkan፣ የምክር ቤት ሊቀመንበር M. Lorena González, የምክር ቤት አባል Teresa Mosqueda, ና የምክር ቤት አባል Tammy Morales የጋራ $45 million የ COVID-19 እፎይታ ጥቅል አሳዉቋል። ከዚህ ጥቅል የፈላሾችና ስደተኞች ጉዳዮች ቢሮ (OIRA) በ COVID-19 የተነሳ የኢኮኖሚ ጉዳት ለገጠማቸዉ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ስደተኛ ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸዉ ድጋፍ ለመስጠት ከከተማዉ አጠቃላይ ፈንድ $9 million የገንዘብ ድጋፍ ተቀብሏል። ይህ ፈንድ የምጨምረዉ $7.9 million ቀጥታ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ በጣም ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸዉ ስደተኛ ነዋሪዎችና ቤተሰቦቻቸዉ የተዘጋጀ የገንዘብ ድጋፍ ነዉ። የቀረዉ $1.1 million ሸሪኮች ጋር ለመድረስ ማህበረሰብ መሠረት ያደረጉ ድርጅቶች ና ሌሎች የቋንቋ ተደራሽነት ተነሳሽነቶች እንግልዝኛ እየተማሩ ያሉ ነዋሪዎች ስለዚህ ፕሮግራም ማወቃቸዉን ለማረጋገጥ ና ሌሎች የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራሞች ና አገልግሎቶች ጥቅም ላይ ይዉላል።

26. ቤተሰቤ በስህተት ሁለት ማመልከቻ ቢያስገባ ምን ይሆናል? በዚያ ምክንያት ብቁ መሆናችን ይቅራል ማለት ነዉ?

ቤተሰብዎ ብዙ ማመልከቻዎችን በህተት ካስገባ Scholarship Junkies ብዙ ማመልከቻዎች ካንድ ቤተሰብ እንደገቡ መለየት ይችላል፤ የበለጠ ፍላጎት የሚያሳይ ማመልከቻን ይመለከታል። ማመልከቻ ላይ ችግር ካዩ አማልካቾችንም በስልክ ወይንም በስልክ አጭር ጽሑፍ መልዕክት ልያገኙ ይችላሉ።

27. አሁንም ጥያቄዎች አሉኝ። በቋንቋዬ ጥያቄዎች ለመጠየቅ የሆነ ሰዉ ጋ መደወል እችላለሁ?

እባክዎን ለድጋፍ ከዚህ በታች ካሉት ድርጅቶች አንዱን ያግኙ፡

 • Community Response Alliance: 206-618-5794

Scholarship Junkies

Seattle COVID-19 Disaster Relief Fund for Immigrants